Hidu ngeru | ሂዱ ንገሩ
Credit to Zemarit Mirtnesh Tilahun
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነሥቷል በዚህ የለም/፪/ መድኃኔ አለም
ሞት የማይችለው የበረታ ኃያል ነው የማይረታ
ማኅተሙን የፈታ የትንሳኤው ጌታ
ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን እምንዘምረው
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው
ዳንን የምንለው
አዝ….
ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘላለም
በመቃብር ሞት ይይዘህ ዘንድ ከቶ አልቻለም
ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ
ከፍ በል በእልልታ
አዝ….
ማቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር
ጌትነትህ ስራህ ይኖራል ሲመሰከር
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ
ዕጹብ ያንተ ስራ
አዝ….
መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና
መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና
ከተማዋ አንዳች ሁናለች በሌሊቱ
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ
ከበረውን ምቱ
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነሥቷል በዚህ የለም/፪/ መድኃኔ አለም
ሞት የማይችለው የበረታ ኃያል ነው የማይረታ
ማኅተሙን የፈታ የትንሳኤው ጌታ
